የሰላም እሳቤ እና አስፈላጊነት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰላም በኢትዮጵያ በመሠረታዊነት ከአዎንታዊ እሳቤዎች የሚነሳ፣ ከሀገራዊና ማኅበረሰባዊ ዳራ የሚመነጭ እንደመሆኑ በየጊዜው የሚያድግ እና ዓለምአቀፋዊ ልምዶችን የሚያካትት ስለሚሆን ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎ ች አልፎ አህጉራዊ ሁኔታዎች ጋር በእጅጉ የሚተሳሰር ነው።

የሰላም ግንባታ እሳቤዎች መሠረቱ ከግለሰብ እስከ ማኅበረሰብ፤ ከዚያም ባሻገር ነው ሲባልም መልከ ብዙ ቀጣናዊና አህጉራዊ ግንኙነቶችም ይኖሩታል፡፡ የእርስ በርስ ግንኙነቶች እና ማኅበራዊ ትስስሮች ከአካባቢያዊ የሰላም ሁኔታዎች ጋር ተያያዥነት አላቸው። ማኅበረሰዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መደላደሎች ሊፈጠሩ የሚችሉት የተረጋጋ ሰላም ሲኖር ነውና።

መዋቅራዊ የሰላም ግንባታ ጅምሮችን የሚያጎለብት፣ ማኅበረሰባዊ እሴቶችን ያማከለ፣ እና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያካትት ሰላምን ይበልጥ የሚያፀና ሥራ መሥራት ከሀገራችን ተሻግሮ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ለውጦች ፋይዳው የላቀ ነው።

ሰላምን በመጠበቅ፣ በሁሉም መስኮች ያሉትን የሰላም አበርክቶዎች የሚያጎላ፣ የሚያስተሳስር እና ከተፈጥሮና ከሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎች ጋር የሚስማማ ዕድገትና ለውጥ በማምጣት እና እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለስኬት ለማብቃት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !