አሰባሳቢ ትርክት ለብሔራዊ መግባባት
አሰባሳቢ ትርክት ለብሔራዊ መግባባት
ትርክቶች የተለያዩ ወገኖች ለግልና ለቡድን ዓላማዎቻቸውና ፍላጎቶቻቸው ማሳኪያ በሚሆን መንገድ የሚተረጉሙትና ታሪክን መሠረት ሊያደርጉ የሚችሉ ናቸው፡፡
ትርክቶች ገንቢም አፍራሽም ሊሆኑ ስለሚችሉ ተልዕኮዎቻቸው በምን እሳቤዎች ላይ እንደተመሠረቱ መመርመር፣ በአግባቡ መገንዘብ እና በተለይ ነጠላ ትርክቶች ሊያስከትሉ ከሚችሉ አፍራሽ ተፅእኖዎች መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ነጠላ ትርክቶችን ከመከተል መቆጠብና መዳረሻቸው ወዴት እንደሆነ ማወቅ፣ ምክንያታዊ መሆን ጠቃሚ ነው።
አፍራሽ ትርክቶች በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ጎታች አስተሳሰቦችን ከማስረፅ በተጨማሪ ለምናስባቸው ግለሰባዊ፣ ማኅበረሰባዊና ሀገራዊ ግቦች ስኬትን ሳይሆን ውድቀትን ያመጣሉ።
እንደ ሀገርም እንዲፈጠር የሚፈለገው አንድነትና ብሔራዊ መግባባት በአጭር ጊዜ የተሳካ እንዳይሆን ቀላል የማይባል ተፅእኖ ሊፈጥር ይችላል። ነጠላ ትርክቶች በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ በሀገር ግንባታ፣ በብሔራዊ መግባባት፣ በልማትና ዕድገት የሚያሳርፈትን ተፅእኖዎች መግታት የሚቻለው ገንቢ፣ አሰባሳቢ፣ አቀራራቢ እና ብሔራዊ ማንነታችንን የሚያጎሉ የወል ትርክቶችን በማጎልበት ነውና ይህንን በማድግ በሀገር ገንባታው ላይ ድርሻ ማበርከት አስፈላጊ ነው።
ሰላም ለኢትዮጵያ !