የአብሮነት ሣምንት የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታኅሣስ 25 / 2016 . (የሰላም ሚኒስቴር) ከታህሳስ 20 እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2016 . በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የነበረውየአብሮነት ሣምንትየማጠቃለያ መርሐ-ግብር  ተካሄደ።

  የዘንድሮው የአብሮነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ 26 ጊዜ በሀገራችን  14 ጊዜ "ብዝሃነትን መኖር " በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

በማጠቃለያ  መርሐ-ግብሩ  ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ  የተገኙትን ጨምሮ ከሀገር ውስጥና ከመላው ዓለም 100 ሺህ በላይ ታዳሚዎች ደቦ በተሰኘ ሀገራዊ መተግበሪያ አማካይነት በበይነ መረብ ተሳትፈዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት በጋራ በመሆን መርሃ -ግብሩን አዘጋጅተውታል።