“በጎነት ለአብሮነት”

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ተግባራት መካከል ሀገራዊ አንድነትና ብሔራዊ መግባባትን የሚያጎለብቱ ስራዎችን እንደሚያከናውንና በህብረተሰቡ መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን በመቀየስ እንደሚሰራ ተቀምጧል።

ተቋማችን እነዚህን ተግባራትን ለማከናወን ከነደፋቸው ፕሮግራሞች መካከል ብሔራዊ የሰላም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሙ አንዱ ሲሆን ተቋማችን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ “በጎነት ለአብሮነት” በሚል ፅንስ ሃሳብ በርካታ ወጣቶችን አያሳተፈ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት በ14 ተከታታይ ዙሮች ከ65ሺህ በላይ የሰላም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰልጠን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ማሰማራት ተችሏል።

የብሔራዊ የበጎ ፈቃደ ሥራ በሀገራችን የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው የማንነታችን መገለጫ ነው ፡፡ ለአብነትም የማናውቀው ሰው ወይም እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ ቤት የፈጣሪ ነው ብለን ቤታችን አስገብተን እግር አጥበን ተንከባክበን የምንሸኝ፣ ውሃ ስንጠይቅ ወተት የምንሰጥ ህዝቦች ነን ፡፡ ይህ ክንውን በውስጡ የበጎነት ሀሳብ ያለበት መልካም ተግባር ነው፡፡

በጎ ፈቃደኝነት በነፃ በፍላጎት ህዝብንና ሀገርን ለማገልገል የዕውቀት፣የጉልበት እና የገንዘብ አበርክቶ ማድረግ ሲሆን የበጎ ፈቀድ አገልግሎት ደመወዝ የህዝብ እርካታ እና መንፈሳዊ ሀሴት ማግኘት ነው፡፡ሀገር የተገነባቸው በበጎ ፈቃደኞች መልካም ፈቃድ እና ይሁንታ ሲሆን ዜጎች በሚችሉት አቅም ለሀገራቸው ሰላም እና ልማት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር አንድነት እና ሰላም ሲረጋገጥ የሁሉም ተጠቃሚነት በዚያው ልክ ስለሚረጋገጥ በዚህ ሂደት የምናስቀምጠው አሻራ መልሶ ለራሳችን መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል።

ሰላም ለኢትዮጵያ!