ብሔራዊ የሰላም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ለአወንታዊ ሰላም ግንባታ ያለው ሚና
ብሔራዊ የሰላም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ለአወንታዊ ሰላም ግንባታ ያለው ሚና
የሰላም ሚኒስቴር ሀገራችን ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት እና ሃገራዊ መግባባት የጎለበተባት አገር እንድትሆን ዘርፍ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ተቋሙ ህዝቡን በማሳተፍና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተለያዩ የዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የሀገር ግንባታ ስራዎችን ለመስራት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ብሔራዊ የሰላም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም አንዱ እና ነው።
ይህ ፕሮግራም በታሪክ ሂደት ውስጥ የተፈጠሩ እና የተዛነፉ ትርክቶችን ለማስተካከል ወጣቶችን ከሚኖሩበት አካባቢ ወጥተው ወደ ማያውቁት አካባቢ/ክልል/ በመሄድ የማያውቁትን ማህበረሰብ እንዲመለከቱ፣ ሌላኛውን የኢትዮጵያ ጫፍ በእግራቸው ረግጠው፣ በአቅማቸው አገልግለው የሀገር ፍቅርን እንዲያዳብሩ እና በሂደቱ ደግሞ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ወንድማማችነትን እንዲያጠናክሩ የተቀየሰ እና እየተሰራበት ያለ ፕሮግራም ነው፡፡
ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ተቋማችን አወንታዊ ሰላምን ለማስፈን እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም የሰላም አምባሳደሮች ተፈጥረዋል፣ ህዝቦች ተቀራርበዋል፣ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ዳብረዋል። ፕሮግራሙ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ለማጎልበትና እና የብሔራዊ መግባባት ተግባራትን ለማጠናከር ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ያስመሰከረ ሲሆን ወጣቶች እድል ከተሰጣቸው ሀገራቸውን ለማገልገል እና ወደ እድገት ለመምራት ወሳኝ የማህበረሰብ ክፍሎች መሆናቸውን አሳይተዋል
ሰላም ለኢትዮጵያ!