ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት አደረሰን፣ አደረሳችሁ። አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅር ፣ የደስታና የዕድገት ይሆን ዘንድ ምኞታችን ነው!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የዘንድሮውን አዲስ ዓመት የምናከብረው የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ በተመረቀበት ማግስት በመሆኑ ደስታችን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል።

አዲስ ዓመትን ስናከብር አብሮነትን የበለጠ በሚያጎለብት ሁኔታ በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲከበር እየተመኘን ኢትዮጵያዊያን እንደ ግለሰብ፣ እንደ ቤተሰብ እና እንደ ማህበረሰብ ለጋራ ሰላማችን በጋራ እንቁም በማለት በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ልባዊ ምኞታችንን እንገልፃለን፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!

መልካም አዲስ ዓመት