የኢሚግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሣኝ ኩነት ኤጀንሲ

የኢሚግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሣኝ ኩነት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1ዐ97/2ዐ11 በአዲስ መልክ የተቋቋመ ሲሆን፣ የኢሚግሬሽን፣ የዜግነት፣ የወሣኝ ኩነት እና የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡

ኤጀንሲው ጥራትና ተአማኒነት ያለው የኢሚግሬሽን አገልግሎት በመስጠት፣ የብሔራዊ መተወቂያና ወሣኝ ኩነት ምዝገባ ሥርዓት በመዘረጋት የብሔራዊ ደህንነትን፣ የህግ ማስከበርንና  የማህበራዊ ኢኮኖሚ ልማትን መደገፍን ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡

በእስካሁኑ ክንውንም ለአፍሪካ አገራት የመድረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አገልግሎትን መስጠት በመጀመሩ የተገልጋይ እርካታ እንዲገኝ አስችሏል፡፡ በሌላም በኩል በተለያየ መንገድ የኢሚግሬሽን ህግ የሚተላለፉትን ተገቢው ቅጣት እንዲያገኙ በማድረግ ህግ የማስከበር ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ህገ-ወጥ የሰዎች፣ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታትም ከፌዴራል እስከ ክልል የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የሚሣተፉበት ግብረ ኃይል በማቋቋም የመቆጣጠር ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡