ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ፖሊሲና ስትራቴጂ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር ማድረግና ስትራቴጂክ የመጠባበቂያ እህል ክምችትን መያዝና ማስተዳደር ከዓላማዎቹ መካከል ይጠቀሣሉ፡፡

የመጠባበቂያ እህል ክምችትን፣ ለአደጋምላሽ ሥራ የሚውል የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለዕለት ድጋፍ የሚውል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በመንግሥት የግዢ ሥርዓት መሠረት ከአገር ውስጥ ወይም የውጭ አገር ይገዛል፣ በዕርዳታ ይቀበላል፣ በክምችት ይይዛል፣ ያስተዳድራል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሣ፣ የአደጋ ምላሽ እና የአደጋ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ፕሮግራሞች ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡

 

ኮሚሽኑ አገር አቀፍ የአደጋ ሥጋት ፕሮፋይልን በማዘጋጀት የተሟላ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በየደረጃው ይዘረጋል፣ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡ የተዘረጋው ሥርዓትም ተደራሽ፣ ለአደጋ ምላሽ ሰጪና ዝግጁ እንዲሁም ለድንገተኛ ደራሽ አደጋዎች የታቀዱ ዕቅዶች ተግባራዊ መሆን መቻላቸውን ለማረጋገጥ የናሙና ልምምዶች እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡