የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን በሚገኝበት ህጋዊ ቁመናና ተልዕኮ የፖሊሲ ቲንክ ታንክ ሊባል የሚችል ተቋም ነው፡፡ የቲንክ ታንክ ተቋማት በፐብሊክ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የአገርንና የሕዝብን ጥቅም ወግነውና መነሻ አድርገው ጥናታዊ ምርምር የሚያከናውኑ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር የነበረ ሲሆን፣ የሠላም ሚኒስቴር ከተቋቋመ በኋላ ተጠሪነቱ ለሠላም ሚኒስቴር ሆኗል፡ ተቋሙ ኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥታዊ ያደረገቻቸው የዜጎች መብት መከበር ጉዳዮች ይበልጥ ሥር እንዲሰድ፣ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ እንዲጎለብትና የኢኮኖሚና የሶሻል ዕድገት እንዲፋጠን የሚረዳ ጥናትና ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባሻገር አገራችን ሠላሟ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ ከሠላም ጋር የተያያዙ ባለድርሻ አካላትን ማወያየትና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋት ላይ ይሠራል፡፡

ከዚህም ባሻገር አገራችን ከጎረቤት አገሮችና የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ያላት ሠላማዊ ግንኙነት እንዲጎለብትና መነሻቸው ሌሎች አገሮች የሆኑ የሠላም ጠንቆችን በመለየትና በማጥናት በውጭ ግንኙነት ዙሪያ ምክረ ሃሣብ የሚሰጥ ኢንስቲትዩት ነው፡፡