በጅግ-ጅጋ ከተማ የጋራ ምክክር መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መጋቢት 14/2016 . የሰላም ሚኒስቴር ከሱማሌ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመቀናጀት ከክልሉ ሰባት ዞኖችና ከጅግጅጋ ከተማ  አስተዳደር የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ ዑላማዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የወጣትና ሴቶች አደረጃጀ፣ የሰላምና ፀጥታ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የነጋዴ /ቤት፣ የምሁራን /ቤት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ ውስጥ የተጀመረው ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው በጅግ-ጅጋ ከተማ የጋራ ምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

 

የክልሉ ሰላም ለማጠናከርና መንግሥትና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሠርተው ያመጡትን ለውጦች በተሞክሮ ለመቀመር እንዲሁም በምሥራቁ ነባራዊ ሁኔታ ከጎረቤት ሀገሮች የሚታዩ ምልክቶችን/እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡

 

የሱማሌ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ደይብ አህመድ ኑርክልላችን ለውጡን ተከትሎ ሰላምን ለመፍጠር በሠራቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ከተመዘገቡት ስኬቶች አንዱ የተሻለ ሰላም መፈጠሩ ነው፡፡ የክልሉ መንግሥት ከሕዝብ ጋር በትብብር በመሥራት ሰላምን ለማረጋገጥ የወሰደውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ነው፡፡ ውጤቱ በዋናነት ከሕዝብ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የመጣ ሲሆን ከሃይመኖት አባቶች፣ ዑጋዞች፣ ዑላማዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የወጣትና ሴቶች አደረጃጀት እና ሌሎች የሰላምና ፀጥታ አመራሮች እንዲሁም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ መሥራት በመቻሉ የመጣ ነውብለዋል፡፡ የሱማሌ ክልል ካለበት ልዩ ጂኦ-ፖለቲካል አኳያ ለክልሉ ሰላም መስፈን ድጋፍና እገዛ ላደረጉ ለሰላም ሚኒስቴር፣ ለመከላከያ ሚኒስቴር፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

መድረኩን በይፋ የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (/) “የሱማሌ ክልል ሰላም ከሕዝብ በመነጨ የሰላም ፍላጎት እና የጋራ ተሳትፎ በተሠራ ጠንካራ ሥራ የተገኘ ውጤት ነው፡፡ ክልሉ የሰላም ግንባታ ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ ከሕዝብ ጋር በቅንጅት መሥራቱ በሂደቱ ለተሳተፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የሰጠው ዕውቅና የሰላም ሚኒስቴር በልዩ አድናቆት የሚመለከተውና ይህ ተሞክሮውም በሌሎችም የሰላም ችግሮች በሚታዩባቸው አካባቢዎችም አጋሮችን አሳትፈን ተግባራዊ ካደረግን ውጤት የምናመጣባቸው ይሆናሉብለዋል፡፡

 

በክልሉ የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ክልሉ በዚህ ረገድ የሠራው ሥራ ከሌሎች የሀገራችን አካባቢዎችም ባሻር ለጎረቤት ሀገሮች ሰላም የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከክልሉ ውጪ ከጎረቤት ሀገሮች የሚመነጩ አልፎ አልፎ የሚታዩ አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ የምሥራቅ አፍሪካን ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡ ሰላምን ለማምጣት ዋጋ የተከፈለባቸውን ልምዶች በማጠናከር እና ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን እውን ለማድረግ የጋራ ትብብርና ቅንጅት አጠናክሮ ማስቀጠል የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረውም ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ ለክልሉ አመራር እና የፀጥታ ባለሙያ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጎሣ መሪዎች፣ ዑላማዎች እና ሌሎችም ምስጋና የሚቸራቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።