የአብሮነት ሣምንት የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ተካሄደ
የአብሮነት ሣምንት የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ተካሄደ
ታኅሣስ 25 / 2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) ከታህሳስ 20 እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የነበረው “የአብሮነት ሣምንት” የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ተካሄደ።
የዘንድሮው የአብሮነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ14ኛ ጊዜ "ብዝሃነትን መኖር " በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙትን ጨምሮ ከሀገር ውስጥና ከመላው ዓለም ከ100 ሺህ በላይ ታዳሚዎች ደቦ በተሰኘ ሀገራዊ መተግበሪያ አማካይነት በበይነ መረብ ተሳትፈዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት በጋራ በመሆን መርሃ -ግብሩን አዘጋጅተውታል።