የሰላም ሚኒስቴር በጎፋ ዞን ለተጎዱ ወገኖች ለመልሶ ማቋቋም የሚረዳ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ ለተጎዱ ወገኖች ለመልሶ ማቋቋም የሚረዳ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በጎፋ ዞን ለተጎዱ ወገኖች ለዕለት ደራሽ ሰብዓዊ ረድኤት እንዲሆን በዓይነት 4.2 ሚሊዮን ብር የሚገመት እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ 2.2 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ የ6.4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም በሳውላ በመገኘት ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ፤ ሚኒስቴሩ በቀጣይም ለመልሶ ማቋቋም የሚውል ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

አቶ ብናልፍ በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፤ ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እየሰራ ካለው ሰፊ ስራ በተጓዳኝ  መሰል ተፈጥሮአዊ አደጋ ሲደርስ ግዴታውን ይወጣል ብለዋል። 

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አሁን ላይ መላ ኢትዮጵያዊውያን ለተጎጂዎች እያደረጉ ያለውን ድጋፍ በጎ መሆኑን አድንቀው፤ ከዚህ በኋላ በዋናነት በአደጋው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ማቋቋም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።