የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የዛምቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር የሆኑትን ጃኮብ ጃክ ምዊቡን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2016 . የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የዛምቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር የሆኑትን ጃኮብ ጃክ ምዊቡን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት  በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ያብራሩ ሲሆን በቀጣይም ያጋጠሙ ችግሮችን በውይይትና በመነጋገር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገራችንን ልማት ከማረጋገጥ አንጻር በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በግብርና፣ በአረንጋዴ አሻራና በአይ ሲቲ ዘርፍ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ መንግስት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ክቡር አቶ ብናልፍ አክለውም ህገ- ወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመቀነስና በህጋዊ መንገድ እንዲሔዱ በማድረግ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን ሞት፣ ስቃይና እንግልት ለማስቀረት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እየተሰራ መሆኑን  ገልፀዋል። ተጨማሪም የዛምቢያ መንግስት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

የዛምቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ጃኮብ ጃክ ምዊቡን  በበኩላቸው በዛምቢያና በኢትዮጵያ ሀገራት መካከል የቆየ ግንኙነትና ትብብር እንዳለ  ያነሱ ሲሆን የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ አገዛዝ ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም ያላቸውን ክብርና አድናቆት ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በሰላምና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ሃሳብ ገልጸው፤ በተለይ ሀገራቸው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መተላለፊያ መንገድ እንደመሆኗ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን - ሰብአዊ ድርጊትና እንግልት በዘላቂነት ለማስቀረት በትብብርና በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አክለውም በደቡብ ኢትዮጵያ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን ገልጸዋል፡፡

መጨረሻም ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ በማጠናከርና የጋራ የመረጃ ልውውጥ ስርአት በመዘርጋት የአፍሪካን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ብሎም የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን ለመፍታት ከምን ጊዜውም በላይ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡