የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴሬሽን ምክርቤት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል
የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴሬሽን ምክርቤት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል
ነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር የሀገራዊ ለውጡ ዋና ዓላማ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ፣ ሀገራዊ ልማትን ማረጋገጥና ዲሞክራሲን ማስፈን እንደሆነ ገልፀው ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የሁለቱ ተቋማት ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው የሰላም ግንባታ ስራ አንድ ተቋም ብቻ የሚሰራው እንዳልሆነ ገልፀው ዛሬ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው ስምምነት ተቋማቱ በቅንጅት በመስራት ዘላቂ የሰላምን ግንባታ ስራችንን የበለጠ የተሳካ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ስምምነቱን የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ትግሉ መለሰ ተፈራርመዋል ፡፡