"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" የፎቶ አውደ-ርዕይ
"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" የፎቶ አውደ-ርዕይ
"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገው አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ የስዕል አውደ ርዕይ ለእንግዶች ክፍት ሆኗል።
የስዕል አውደ ርዕዩ በኢፊዴሪ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ታዬ አፅቀሥላሴ የተከፈተ ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ክቡራን ሚኒስትሮች፣ ክቡራን የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ክቡራን አምባሳደሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።