" ወጣቶችን ያማከለ የፀረ- ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል " በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ
" ወጣቶችን ያማከለ የፀረ- ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል " በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ
ኅዳር 26 ቀን 017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች "ወጣቶችን የማከለ የፀ-ረሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ሃሳብ ለ21 ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በደማቅ ዝግጅት አክብረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር ) ሙስና ለሀገራችን ሰላም እና ልማት ትልቅ ተግዳሮት ነው ያሉ ሲሆን የፀረ ሙስና ትግል የሁሉንም ተሳትፎ እና እርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።
የዘንድሮ የፀረ ሙስና ቀን ወጣቶችን ያማከለ አድርጎ መከበሩ ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ክቡር ከይረዲን ተዘራ ወጣቶችን ለፀረ ሙስና ትግል እና ለሀገር ግንባታ ስራችን ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።
'' ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ'' የሚል ሰነድ የሰላም ሚኒስቴር የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ አበራ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የአንድ ሀገር ቀጣይነት የሚረጋገጠው ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማት ሲኖሩ መሆኑን ገልፀው የአገረ መንግስቱ አንዱ ቁልፍ ችግር ነፃ፣ ገለልተኛና ማህበረሰቡን የሚጠብቁ ተቋማት ሳይገነቡ መቆየታቸውን ገልፀው በዚህ በኩል መንግስት ትልልቅ ሪፎርሞችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ሙስናን ለመታገል ጠንካራ ተቋማት እና የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት ክቡር አቶ ቸሩጌታ ሙስናን መታገል ንብረትን ከዘረፋ እና ብክነት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሀገር የመገንባት ስራ ነው ብለዋል።