ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብን እንዲሁም የጎንደር አብያተ መንግሥታት ቅርስ እድሳትንና የኮሪደር ልማትን ጎብኝተዋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብን እንዲሁም የጎንደር አብያተ መንግሥታት ቅርስ እድሳትንና የኮሪደር ልማትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና ሌ ሎችም ተሳትፈዋል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር መሐመድ እድሪስ ህዝቡ ለሰላም በከፈለው ዋጋ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው እየተፈቱ መሆኑን የጎበኘናቸው ፕሮጀከቶች የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

ያለ ሰላም የመሠረተ ልማት ግንባታ እና የቅርስ ጥበቃ ማድረግ እንደማይቻል ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ጎንደር በአንጻራዊ ሰላም ላይ የምትገኝ በመሆኗ የከተማዋን ሕዝብ የልማት ጥያቄ ለመፍታት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

 

በከተማዋ አሁን ያለውን አንጻራዊ ሰላም በማጽናት የጎንደርን ልማት ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጎንደር የኢትዮጵያ ቀደምት ሥልጣኔ መነሻ፣ የአብሮነት መገለጫ፣ የአባቶች አሻራ የኪነ ሕንጻ እና ጥበብ መገኛ መሆኗን አንስተዋል።

ጎንደር በራስ ማንነት የተገነቡ ኪነ ሕንጻዎች መገኛ ናት ያሉት ዲያቆን ዳንኤል፤ የአብያተ መንግሥቱ እድሳት በራስ አቅም መሥራት እንደሚቻል ያሳየንበት ነው ብለዋል።

ቅርሱ ለዘመናት ተረስቶ እድሳት ሳይደረግለት መቆየቱን አንስተው፤ የቅርሱ መታደስ የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ እና የጎብኝዎችን ቆይታ በማራዘም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።

እድሳቱ የትውልድ ቅብብሎሽ የታየበት የኋላ ታሪክን ከአሁኑ ትውልድ ጋር የምናስተሳስርበት አሻራ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።