የሞሮኮ ልዑክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ጉብኝት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 15  2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሞሮኮ ልዑክ በአዲስ አበባ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን በመጎብኘት ላይ ይገኛል።

እስካሁን ባደረጉት ጉብኝት የታላቁ አንዋር መስጊድ፣ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንሲልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ቤተ እምነቶች በሰላም እና አብሮነት ለጋራ ሰላም የሚሠሯቸው ሥራዎች በብዙ ልምድ የሚወሰድባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት በሃይማኖት፤ ሃይማኖትም በመንግሥት ጣልቃ ሳይገቡ ለሰላም ፤ ለሀገር እና ለሕዝብ በጋራ የሚሠሩበት ሁኔታ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ ይህም ሃይማኖታዊ ተቃርኖ የሌለውና የሚበረታታ መሆኑን አመላክተዋል።

 

በዕለቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔን ጎብኝተው ከአመራሮቹ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።