የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር የሆኑትን አቶ አኒል ኩማርን ተቀብለው አነጋገሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መጋቢት 8/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ እና የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበር፣ በግጭት አስተዳደር እና በብዝሃነት አያያዝ ዙሪያ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ከሆኑት አቶ አኒል ኩማር ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

የሰላም ሚስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ህንድ እንደ ኢትዮጵያ ብዝሃ ማንነት ያለባት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው በዴሞክራሲ፣ በፌዴራሊዝም ስርዓት፣ በግጭት አስተዳደር እና በብዝሃነት አያያዝ ዙሪያ ኢትዮጵያ ከህንድ ብዙ ልምዶችን ትወስዳለች ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር ያሉብንን ሀገራዊ ችግሮች ተወያይተን እና ተመካክረን በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ ሀገራዊ ምክክር እየተደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን ለማረጋገጥ እና በአጋርነት ላይ የተመሰረተ ልማትን ለማጎልበት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራች እንደምትገኝ አብራርተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም ስርዓት እንዲጠናከር እና የግጭት አስተዳደር ስርዓት እንዲዘምን ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው የዛሬው ውይይትም የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አቶ አኒል ኩማር ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ህንድ እና ኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ግንኙነት ያላቸወ ሀገራት መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ኢትዮጵያ በየጊዜው እያጋጠሟት ያሉትን ችግሮች የምትፈታበት መንገድ እና አዲስ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት የምታደርገውን እንቅስቀሴ አድንቀዋል፡፡ በቀጣይም በፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበር፣ በግጭት አስተዳደር እና በብዝሃነት አያያዝ ዙሪያ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር አብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡