የአፋርና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር በሰመራ እየተካሄደ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር እና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢፍጣር መርሐ ግብሩ የሁለቱ ክልሎችን አብሮነት የሚያጠናክር፣ ወንድማማችነት የሚያጎለብትና ለዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና ለሕዝቦች መቀራረብ ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የኃይማኖት አባቶች የተሳተፉበት የኢፍጣር ፕሮግራም መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በጅግጅጋ መካሄዱ ይታወሳል።

#FBC