የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና አባላት በሰላም ሚኒስቴር በመገኘት የሥራ ምልከታ አደረጉ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና አባላት በሰላም ሚኒስቴር በመገኘት የሥራ ምልከታ አደረጉ
ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስና ሚኒስትር ዴዔታዎች በተገኙት በሰላም ሚኒስቴር በመገኘት የሥራ ምልከታ አድርገዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት የሰላም ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያራምደው አጠቃላይ ስትራቴጅ ምን እንደሚመስል፣ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰላም ግንባታ ስራዎችና የግጭት መከላከልና ቀድሞ የማስጠንቀቂያ ስርዓት ጋር በተያያዘ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ለመከላከልና ቀድሞ የማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ለመሰብሰብና ለመተንተን ምን ዓይነት ስርዓት እንዳለው ምልከታ አድርገዋል ።
በተለይም የሰላም ሚኒስቴር የገነባውን የግጭት ማስጠንቀቂያና ምላሽ ክፍልን/Situation room/ አሰራርን በጥልቀት ተመልክተዋል።
በተጨማሪም አባላቱ የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን ፣ የሰራተኞች የሥራ አካባቢ፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች፣ የሰራተኞች ደህንነት አጠባበቅ፣
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የሰው ኃይል አቅም ፣ከክልሎች ጋር ያለዉ ትስስርና አሰራር ሂደትን አይተዋል።
የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
ክቡር አቶ መሀመድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት በተቋሙ ተገኝተው የደረጉትን ምልከታ አድንቀው እንደዚህ ዓይነት ክትትል እና ድጋፍ ለቀጣይ ሥራዎች መሠረት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና አባላት የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ እደመጡ የተናገሩ ሲሆን በቀጣይም የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።