''የመሀሉ ዘመን'' በሚል ወቅታዊ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ
''የመሀሉ ዘመን'' በሚል ወቅታዊ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ
ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ''የመሀሉ ዘመን '' በሚል ወቅታዊ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ሀገራችን ረጅም የፖለቲካ ታሪክ ያላት በዚህ ውስጥ ስኬትም ውድቀትም ያለፈች እና የፀናች ሀገር ናት ።
ከሰባት አመት በፊት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከተቀመጡ የለውጥ ምዕራፎች ውስጥ አሁን ላይ ኢትዮጵያ የመሀሉ ዘመን ላይ መሆናችንን የገለፁት ክቡር አቶ መሀመድ በዚህም ፈተናወችን በማለፍ እና እንደ እድል በመጠቀም የላከ ስኬት የተመዘገበበት እንደሆነ አመላክተዋል። ስለሆነም የመሀሉ ዘመን ወደ ቁልቁለት የመውረድ ስጋት ያለበት ወይም ወደ ላይ የመስፈንጠር ዕድል ያለው ዘመን መሆኑን በመገንዘብ እና የመሀል ዘመን ወጥመዶችን በማለፍ ወደ ከፍታው መስፈንጠር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
''የመሀሉ ዘመን'' በሚል ርዕስ የውይይት ፅሁፍ ያቀረቡት የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ መሀመድራፊ አባራያ ''የመሀሉ ዘመን'' የኢትዮጵያን መነሻ፣ አሁን ያለንበትን ሁኔታ እና የቀጣይ መዳረሻችንን የሚያሳይ የሽግግር ዘመን ነው ብለዋል።
አክለውም የመሀሉ ዘመን የፈተና እና የዕድል ዘመን መሆኑን ገልፀው ያለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስኬቶች የታዩበት፣ መዋቅራዊ ለውጥ /Structural reform/ የተደረገበት መሆኑን ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ያላቸውን አስተያየትና ጥያቄ አቅርበው በመድረክ ማጠቃለያ ተሰጥቶበታል፡፡
ለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡት ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ያስመዘገብናቸው ውጤቶች መዘናጊያ ሳይሆን በበለጠ ሃይል ወደ ቀጣይ ከፍታ ለመሄድ መንገዶች ሊሆኑ ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም እንደ ተቋም የመሀሉን ዘመን ወደ ከፍታ ለመውሰድ የሚፈጠሩ አለመግባበቶችን በራሱ በሰላማዊ መንገድ የሚፈታ እና ለሰላም ዘብ የሚቆም ማህበረሰብ መገንባት እንሚገባ አመላክተዋል፡፡