የሰላም ሚኒስቴር መቀመጫውን አሜሪካ ሀገር ካደረገው ኢስተርሊንግ ፋውንዴሽን ልዑክ ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ተወያየ
የሰላም ሚኒስቴር መቀመጫውን አሜሪካ ሀገር ካደረገው ኢስተርሊንግ ፋውንዴሽን ልዑክ ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ተወያየ
ግንቦት 4/2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከስተርሊንግ ፋውንዴሽን የልኡክ ቡድን ተወካዮች ጋር በሰላም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ተቋሙ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እነዚህ የሃይማኖት ተቋማት ነጻነታቸውና መብታቸው ተጠብቆ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍ በልማትና በሰላም ዙሪያ መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፡፡
አያይዘውም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (LDS),) አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ማስረከቡ በሐይማኖቶች መካከል ያለውን የመደጋገፍ ፣የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ ያሳያል ያሉ ሲሆን ፣ ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ቀጣይም የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም እምነታቸውን ገልጸዋል ።
የስተርሊነግ ፋውንዲሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ፕሬዚዳንት ኒኮል ስተርሊን ( Nicole Sterling) የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር ለሰላም ግንባታ ስራዎች እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ርብርብ አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን እነዚህ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ስተርሊነግ ፋውንዲሽንና ቤ/ክርስቲያኗም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
ስተርሊንግ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረጉ የሰላም ግንባታ ስራዎች በርካታ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበርም በሀገራችን ውስጥ በተፈጥሮ ምክንያት በዜጎቻችን ላይ ለደረሰው ጉዳት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።