13ኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 04/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ13ኛው ዙር ፕሮግራም ለሀያ ሁለት ቀናት በጅግጅጋ ዮንቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ከሰባት መቶ በላይ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ እና የእለቱ የክብር እንግዳ አምባሳደር እሸቱ ደሴ "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው የወጣቶች በጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አግልግሎት መርሃ ግብር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን እና መርሆዎችን ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በሌሎችም ማንነቶች ላይ መሠረት አድርጎ ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ የወጣቶችን የሀገር እና የሕዝብ ፍቅር ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር እሸቴ አክለውም "በዛሬው እለት የስልጠና ጊዜያችሁን አጠናቃችሁ ስምሪት የሚሰጣችሁ ማህበረሰቡን ለማገልገል ስንቅ ሊሆናችሁ የሚችሉ ስነምግባር፣ እውቀትና ክህሎት እንዳገኛችሁ እገነዘባለሁ ብለዋል።

ስለሆነም በስልጠና ያገኛችሁትን እውቀትና ክህሎት በቀጣይ ወራት አገልግሎት በምትሰጡበት ወቅት ትክክለኛ ማንነታችሁን የምታገኙበትና ለቀሪ ህይወታችሁም ስንቅ የሚሆን ማንነት ግንባታ መሆኑን በመገንዘብ በዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ስራ ውስጥም የራሳችሁን አሻራ እንድታሳርፉ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዚዳንት አብዲ ሀሰን (ዶ/ር) የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው "እኛ ኢትዩጵያዉያን ፣ በርካቶች የሚመሰክሩት ፣ ከአለም ሀገሮች የሚለይ ባህል እሴት እና ማንነት ያለን ሲሆን ፣ ይህንን እሴታችንን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ቢሆንም ከወጣቶች ብዙ ይጠበቃል" ብለዋል።

በሀገራችን ያሉ አለመግባባቶችን በመተው ዘላቂ ሰላምና አንድነትን ማጠናከር በልማት ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በምርምርና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ ባህል ልናዳብር ይገባል፤ ያሉት ዶ/ር አብዲ ከናንተ ብዙ የሚማሩ በብዙ ናቸውና የሰጠቻችሁን ሀላፊነት እና የዜግነት ግዴታችሁን በሙሉ ኢትዮጵያዊ ልብ እንድትተገብሩ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡