''የህብረተሰቡን የምክክር ባህል በማሳደግ የተገኘውን ሰላም የማጽናት ስራ እየተሰራ ነው'' ወንድወሰን መኮንን
''የህብረተሰቡን የምክክር ባህል በማሳደግ የተገኘውን ሰላም የማጽናት ስራ እየተሰራ ነው'' ወንድወሰን መኮንን
ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ በሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በመገምገም የታዩ ክፍተቶችን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት ዘላቂ ሰላምን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በመግባባት ተጠናቋል።

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዎች በተገኙበት በሀገራችን የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ በጥልቀት መክረዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን መኮንን በሁሉም ክልሎች በ2017 በጀት ዓመት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የምክክር መድረኮች መካሄዳቸው ህብረተሰቡ ያጋጠመውን ችግሮች በራሱ እንዲፈታና ሀገር በቀል መፍትሄዎችን እዲሰጥ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል ፡፡ እንዲሁም የህብረተሰቡን የምክክር ባህል በማሳደግ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ነው የገለጹት።
አቶ ወንድወሰን አክለውም በቀጣይ በጀት አመትም አስቀድሞ ግጭትን መከላከል ላይ፣የማህበረሰብ ተኮር ምክክርን ማጠናከር፣የባለድርሻ አካላት ምክክርን ማጠናከር እና በግጭት አፈታት ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮ ያላቸውን በማስፉት ዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎችን የሚያጎለብቱ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።