የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከዩኤንዲፒ (UNDP)፣ ዩኤንኤችሲአር (UNHCR) እና ከጃፓን ኢምባሲ(Japan Embassy) ልዑክ ጋር ተወያዩ
የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከዩኤንዲፒ (UNDP)፣ ዩኤንኤችሲአር (UNHCR) እና ከጃፓን ኢምባሲ(Japan Embassy) ልዑክ ጋር ተወያዩ
ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ እና የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ከዩኤንዲፒ (UNDP)፣ ከዩኤንኤችሲአር (UNHCR) እና ከጃፓን ኢምባሲ(Japan Embassy) ልዑክ ጋር ከፍተኛ የአየር ንብረት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች መፈናቀልን የመቋቋም አቅምን ማጎልበት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ (Enhancing Climate Resilience of Displacement Affected communities in high risk areas of Ethiopia Project) ዙሪያ አብሮ ለመስራት በሚያስችል የፕሮጀክት ሀሳብ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የትኛውም ፕሮጅክት ለመስራት ሲታቀድ የሰላም ግንባታ ሃሳብ እና ትግበራ ሊካተት ይገባል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይትም በአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሊሰራ በታቀደው ፕሮጀክት ላይ የሰላም ስራ እንዲካተት እና በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመድረስ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ከዩኤንዲፒ (UNDP)፣ከዩኤንኤችሲአር (UNHCR) እና ከጃፓን ኢምባሲ(Japan Embassy) የተገኙ አመራሮችም ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የታቀደው ፕሮጅክት እንዲሳካ የሰላም ሚኒስቴር ድጋፍ ያስፈልገናል ያሉ ሲሆን ሚኒስቴሩ በሰጣቸው ምላሽም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡