''እንደ ሀገር የሚያስተሳስረን የጋራ ግብ እና የጋራ እጣ ፈንታ ያለን ህዝቦች ነን፤ የአንዳችን እጣ ፈንታ የሌላችንን እጣ ፈንታ ይወስናል '' ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ለአመራሮችና ሰራተኞች ችግሮችን ተቋቁሞ ስለመስራት /Individuals and organizational Resilience/ ላይ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና አጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ እንደ ሀገር የሚያስተሳስሩን የጋራ ግብ እና የጋራ እጣ ፈንታ ያለን ህዝቦች ነን ያሉ ሲሆን የአንዳችን እጣ ፈንታ የሌላችንን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከሀገራዊ ዓላማ እና ግብ የተቀዳ ሀሳብ ይዞ የተቋቋመ ተቋም ነው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው ተቋሙ ለዘመናት ከኖርንበት የግጭት አዙሪት ወጥተን ፖለቲካዊ ልዩነቶቻችንን በመግባባትና በውይይት ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ይህንም በላቀ ሁኔታ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሀገራችንን ሰላም በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ያሉ ሲሆን የሰላም ሥራዎችን የሚያሳልጡ የሰላም አደረጃጀቶችን በየደረጃው መገንባት እና የማህበረሰቡን ማህበረ ባህላዊ ሃብቶች ከፍ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የተጣለብንን ሀገራዊ ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት እያንዳንዳችን የምንሰራው ሥራ ለተቋማችን ግብ መሣካት አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል ያሉት ክቡር አቶ ቸሩጌታ ለተቋማዊ ብሎም ለሀገራዊ ዓላማ መሣካት መተባበር ፣መቀናጀት እና ትስስር መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

በስልጠናው ሲሳተፉ የቆዩ አመራሮች እና ሰራተኞች ስልጠናው ለግል ህይወታቸውና ለተቋማቸው ውጤታማነት የሚሆን ቁምነገሮችን ያገኙበት መሆኑን ገልፀው እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።