“በጎ ፈቃደኞች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በማጽናት ባከናወናችሁ ታላቅ ተግባር የሀገር ባለውለታ ናችሁ፡፡” የተከበሩ ዶ/ር አምባሳደር የሺመብራት መርሻ
“በጎ ፈቃደኞች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በማጽናት ባከናወናችሁ ታላቅ ተግባር የሀገር ባለውለታ ናችሁ፡፡” የተከበሩ ዶ/ር አምባሳደር የሺመብራት መርሻ
ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ ብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት በሀገሪቱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እያጠናከረ መሆኑ ተገለፀ
የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ከተጀመረበት አንስቶ ለወጣቱ የጋራ ታሪኮችን እና የጋራ ማንነትን የሚያውቅበትን ዕድል በመፍጠር አብሮነት እያጠናከረ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር የተከበሩ ዶ/ር አምባሳደር የሺመብራት መርሻ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል፡፡

የተከበሩ ዶ/ር አምባሳደር የሺመብራት የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ፖሊሲ ተቀርፆለት በራሱ መዋቅር የሚመራ ተቋም ሆኖ እንዲቋቋም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክረ ሃሳብ መቅረቡን ጠቁመዋል።
ፕሮግራሙ ወጣቶችን ለቀጣይ ሀገራዊ ኃላፊነት የሚያዘጋጅና የበጎ ፈቃድ ተግባር ማኅበረሰባዊ መሠረት እንዲኖረው የሚያደርግ ውጤታማ ጅምር መሆኑን የገለጹት ደግሞ በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ የሆኑት ክቡር አምባሳደር እሼቱ ደሴ ናቸው፡፡
