ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዚያ 7/2016 ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ  በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ(/) ሰላምን ለማስፈን  ሀይማኖቶች  ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው እንደዚህ አይነት ጉባኤዎች ማካሄድ ዓለም አቀፍ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በንግግራቸው የሀይማኖት ተቋማት ድንበር የለሽ መሆናቸውን አንስተው በጉባኤው ጠቃሚና ተጨባጭ ልምዶች እና ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ -ፍታዊነትን የምንቃወምበት ነው ብለዋል።

 

በጉባዔው ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የሃይማኖት መሪዎች፣  አምባሳደሮች፣ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

 

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ  ክብርን መጠበቅ፣ አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል።