
የሰላም ሚኒስቴር ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሰላምን እንደ ሀገራዊ እሴት በአሁን እና በመጪው ትውልድ አዕምሮ ውስጥ እንዲሰርፅ ይሰራል።
ተጨማሪ ያንብቡ
ሰላም ለኢትዮጵያ ዕድገት፣ አንድነት እና ዘላቂ ልማት መሠረት ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ሰላምን እና ማህበራዊ ትብብርን ማጠንከር የጋራ ብሔራዊ ኃላፊነታችን ነው።
በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሠረት፣ የሰላም ሚኒስቴር ሰላምን ማረጋገጥ እና ማስጠበቅ፣ ግጭትን መከላከል እና ማስተዳደር፣ የፌደራል እና የክልል ክልል ግንኙነትን ማጠናከር እንዲሁም አካታች እና አዎንታዊ ስልቶችን በመጠቀም ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር ከተሰጡት ዋና ዋና ኃላፊነቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።
ሰላም የሚጀምረው ከግለሰብ ሲሆን በቤተሰብ እና በማኅበረሰብ ውስጥ አድጎ ሀገርን ይቀርፃል። በውይይት፣ በምክክር እና እርስ በርስ በመከባበር እንዲሁም በዲጂታል ፈጠራ የተጠናከረ አጋርነት በመፍጠር ጠንካራ ተቋምን በመገንባት አንድነቷ የተጠበቀ ፤ ሰላማዊ ኢትዮጵያን ለአሁኑ እና ለወደፊቱ ትውልድ በጋራ እንሰራለን።
ሰላም ለኢትዮጵያ!