የጅቡቲ፣ የሩዋንዳ ፣የቡርንዲ ፣የላይበሪያ ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገቡ
የጅቡቲ፣ የሩዋንዳ ፣የቡርንዲ ፣የላይበሪያ ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገቡ
የሰላም ሚኒስቴር ኅዳር 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም "የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሃሳብ ላዘጋጀው አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ የሩዋንዳ ፣የቡርንዲ ፣የላይበሪያ ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ኅዳር 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም "የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ለሚያካሂደው አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ የተለያዩ ሀገራት እንግዶች አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛል።
"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ለሀገራችን የገፅታ ግንባታ ከሚጫወተዉ ሚና በተጨማሪ አገራችን የራሷን የሰላም ቁርጠኝነትና ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የምታጋራበት መድረክ ነዉ፡፡በኮንፈረንሱ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ተቋማት፣ የክልሎች ቢሮ ኃላፊዎች፣ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ይሳተፋሉ፡፡