በ14ኛ ዙር መርሃ ግብር በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የሰላም በጎ ፈቃደኞች የምረቃ ፕሮግራም ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በ14ኛ ዙር መርሃ ግብር ተመዝገበው በጅማ፣ በሐዋሳ፣ በወሎ፣ በወልቂጤ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የሰላም በጎ ፈቃደኞች የምረቃ ፕሮግራም ተካሄደ።

የሰላም ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት ለተከታታይ 13 ዙሮች ከ60 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሰልጠን በመላው ሀገርቱ ስምሪት በመስጠት ውጤቶችን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን የበጎ ፈቃደኞችን የአስተሳሰብ ለውጥ መምጣቱ፣ የሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎችን በማወቅ ማህራዊ ትስስርን መፈጠሩ፣ የስራና ፈጠራ ክህሎት ማደጉ፣ ብዘሃነትን እንደ ዕድል መቁጠር መጀመሩ፣ የሀገር ፍቅር ማደጉ፣ የሰላም አምባሳደሮች መፈጠራቸው፣ የበጎነትና አብሮነት ተግባር እየጎለበተ መምጣቱ፣ በብቃታቸውና ስነ-ምግባራቸው የተሻሉ ዜጎችን ማፍራት ከመቻሉም ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፆ አበርክተዋል፡፡

በ14ኛው ዙር መርሃ ግብር 3580 ወንድ እና 2102 በድምሩ 5682 የሰላም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት የምረቃ ስነ ስነስርዓታቸው ተከናውኗል።