አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) "የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሐሳብ አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ለኮንፈረንስ ተካፋዮች ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሰላም በባህሪው በሰው ሰራሽ ድንበር የማይገደብ፤ የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን፣ አፍሪካውያን ለሰላም በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ አለብን ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም እኛ አፍሪካዊያን ብዝኃነታችንን ተጠቅመን ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት ፈጥረን ለችግሮቻችን አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማበጀት የሚሆኑ ሐሳቦችን አቀናጅተን ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰንን መንገድ መቀየስና መጓዝ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም፣ መደማመጥና ከድንበር እና ከርዕዮተ ዓለም በላይ የሆኑ አጋርነቶችን መፍጠር መቻል እና በተባበረ ክንድ ለመጪው ትውልድ የብሩህ ተስፋ መንገድ ለመጥረግ ዛሬ ላይ አህጉራዊ አጋርነትን ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል ።