የሞሮኮ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገባ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 14 ቀን ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) በዶ/ር መሐመድ ረፊቅ የሞሮኮ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ የሚመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ አመራሮች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ክቡር ሚስትር ዴኤታው ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ሀገራችን በረጅም ዘመን ታሪኳ ከተለያዩ ሀገራት እና ሕዝቦች ጋር የነበራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ትስስር እንዲጠናከር በስፋት እየተሠራ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የሞሮኮ ልዑካን ቡድን ከሚያደርገው የሥራ ጉብኝት በተጨማሪ በሀገራቱ መካከል የሚኖረውን የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚያጠናክር መሆኑን አመላክተዋል።

የሞሮኮው የመሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪና የልዑካኑ ቡድን መሪ ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በብዝኃነት የዳበሩ ማኅበራዊ ሀብቶችና ልዩ ልዩ ጥንታዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው የእነዚህም አብሮነት እና መቻቻል ለሀገሮች መልካም ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል ገልፀዋል።

ልዑካኑ በቆይታቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን፣ አንድነት ፓርክና ብሔራዊ ቤተመንግሥትን ጨምሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።