በሱማሌና በአፋር ክልል ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ለማፅናት ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መጋቢት ቀን 2017 ዓም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከሱማሌና ከአፋር ክልሎች ከተወጣጡ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት በሁለቱ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ለማፅናት ያለመ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) መንግስት በሁለቱ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት ተከታታይ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በማጠናከር ወደ ልማት እና ዕድገት መቀየር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የሰላም ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ፀጥታ ተቋማት፣ ከአፋርና ከሱማሌ ክልሎች ጋር በሰራው ከፍተኛ የቅንጅት ስራ በሁለቱም ክልሎች መካከል አንፃራዊ ሰላም መታየቱን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው የሁለቱ ክልሎች ሰላም መሆን ለሁለቱም ህዝቦች ከፍ ሲልም ለሀገር ሰላም መሠረት ነው ብለዋል። ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእስልምና ሐይማኖት ስለ ሰላምና ግጭት አፈታት ያለው አስተምህሮን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።

የሰው ልጅ ክቡር ነው፣ በእስልምና አስተምህሮ የሰው ልጅ የተከበረ ነው ያሉት ደግሞ ኡዝታዝ በድሩ ሁሴን ናቸው። ኡዝታዝ በድሩ እንደ እስልምና አስተምህሮ በጎሳ እና በነገድ ተከፋፍለን የተፈጠርነው እርስ በእርስ እድንተዋወቅ እና እድንረዳዳ ነው ያሉ ሲሆን ልዩነቶቻችን ለመተዋወቅ እንጂ ለመለያየት አይደለም ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከሱማሌና ከአፋር ክልሎች ከተወጣጡ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር እያደረገ የሚገኘው ውይይት እንደቀጠለ ነው።