የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለብሔራዊ ምክክር ኮማሽን ግብዓት የሚሆን አጀንዳ አሰባሰቡ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 15/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር )፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ግብዓት የሚሆን የተለያዩ አጀንዳዎችን አንስተው ተወያይተዋል።

ይህ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን እያደረገ በሚገኘው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ላይ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛው በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሃሳባቸውን እንዲገልፁ እና አካታችነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራችን ያሉ እና የነበሩ ዋና ዋና ችግሮችና መፍትሔዎቸው፣ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ በሀገራችን መሻሻልና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች፣ በሀገራችን ያሉ ግጭቶች መንስኤዎች፣ ተቻችሎ ለመኖርና ተከባብሮ ለመኖር መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች እና ችግሩን ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ምን መስራት አለባቸው በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጀንዳቸውን አቅርበዋል።

 

የተሰበሰበው አጀንዳ ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የፌዴራል ተቋማት የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች የምክክር መድረክ የሚቀርብ ሲሆን ይህን አጀንዳ ተቋሙን ወክሎ የሚያቀርብ ተወካይም ተመርጧል፡፡