የሐገር ሽማግሌዎች ከእኔነት ትርክት ይልቅ አሰባሳቢ ትርክት ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 19/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር "ማህበራዊ ሀብቶቻችን ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችን " በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች እና የማህበራዊ የሰላም ተቋማት አመራሮች የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና የሐገር ሽማግሌዎች ሰላምን ለማፅናት እና ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት የሃይማኖት አባቶችና የሐገር ሽማግሌዎች ሚናንን አስመልክቶ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በተነሳው ሃሳብ ላይ ማጠቃለያ ተሰጥቶበታል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሐገር ሽማግሌዎች የሽምግልና ሥራ ይስሩ ፖለቲከኞች ደግሞ የፖለቲካውን ሥራ ይስሩ ያሉ ሲሆን የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብና መንግስትን የሚያሰታርቁ፣ ገለልተኛ ሆነው ለዕውነት የሚቆሙ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ሽምግልና ከሁሉም ነፃ የሆነ ተቋም ሊሆን ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ የሐገር ሽማግሌዎች ከእኔነት ትርክት ይልቅ አሰባሳቢ ትርክት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የሐገር ሽማግሌዎች አንዳንድ መርዛማ ከሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅኖ ነፃ ሆነው ስራቸውን ሊሰሩ ይገባል ያሉት ክቡር አቶ መሐመድ በምናደርጋቸው ማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ አብሮነትን እና አንድነት ለማጠናከር የሐገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ትኩረት አድርገው ሊንቀሳቀሱ ይገባል ብለዋል፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች ጠንከራ ተቋም ሆነው የራሳቸው የሆነ የህግ ማዕቀፍም ሊኖራቸው እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም ለማጎልበትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሰላም ሚኒስቴር ከሃይማኖት አባቶችና ከሐገር ሽማግሌዎች ጋር በቅርበት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡