ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሁኔታ ማክተም አለበት - አቶ ጌታቸው ረዳ
ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሁኔታ ማክተም አለበት - አቶ ጌታቸው ረዳ
ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሁኔታ ማክተም እንዳለበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።
አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት “ሰላም፣ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎች እና ፈተናዎች” በሚል ሀሳብ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፥ በሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ወጣቱ መምከሩ ብዙ እንዲያተርፍ ያደርገዋል ብለው፤ የጎደለን ነገርን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።
ዘላቂ ሰላምን በክልሉ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ነው ምክክሩ የተደረገው።
መድረኩ በሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፤ በትግራይ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ትኩረት አደርጓል።
በትግራይ የገጠመውን የሰላም እጦት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ መስጠት ዓላማ ባደረገው መድረክ፤ ሁሉም በርብርብ በመስራት በክልሉ ሰላም፣ዲሞክራሲ እና ልማት ማረጋገጥ ይገባል ነው የተባለው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሀኔታ ሊያከትም እንደሚገባ ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ክልሉ ሰላሙን ማረጋገጥ ባለመቻሉ ችግሮች መኖራቸውን በመጠቆም፤ የውይይት መድረኮች ተደርገው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።