“በመትከል ማንሰራራት” ሰባተኛው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ከየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ኑዋሪዎች ጋር በመሆን የካ ተራራ በሚገኘው ቦታ ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በችግኝ ተከላ ቦታው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ/ም የተጀመረ መሆኑን ገልፀው ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በተካሄደው የንቅናቄ ስራ ኢትዮጵያ ለተፈጥሮ የሰጠችው ልዩ ክብር የገለጠ እና ከፍታዋን ለዓለም ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በመትከል ማንሰራራት የሚለው ሃሳብ ሰባት ዓመታትን የተሻገረ የአትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የሚያሳይ እና ለቀጣይ የተሻለ መነቃቃትን የሚፈጥር ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት 3000 ችግኞችን የተከሉ ሲሆን በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ዛፍ እንዲሆኖ ለማስቻል የክትትል ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል፡፡

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ፣ የየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሙሉ ገዳሙ፣የሃይማኖት አባቶች፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች እና የየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡